Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ባለሃብቶች በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣መስከረም 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ባለሃብቶች በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
አሸባሪው እና ዘራፊው የትህነግ ቡድን በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ቁሳዊ እና ሰብዓዊ ጉዳት አድርሷል፡፡ በጉዳቱ በርካታ ወገኖች በግፍ ሲጨፈጨፉ በበርካታ አካባቢዎች ደግሞ ቁሳዊ ዘረፋ ፈጽሟል፡፡
የአማራ ባለሃብቶችም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት በመረዳት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
ዛሬም በጋይንት ግንባር ወገኖቻቸውን በግፍ ላጡ 106 ግለሰቦች ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በመቄት ወረዳ ሃብት ንብረታቸውን ለተዘረፉ እና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች 600 ኩንታል ለዕለት ፍጆታ የሚውል ዱቄት እና ቅንጨ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉን በቦታው ተገኝተው ያስረከቡት የአማራ ክልል ተወላጅ ባለሃብቶች የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ የሎጀስቲክስ ክፍል አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ቢያዝን፥ ድጋፉ የዕለት ደራሽ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ተደራሽ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡
የአማራ ባለሃብቶች አሸባሪው እና ወራሪው የትህነግ ቡድን ጉዳት ባደረሰባቸው በርካታ አካባቢዎች ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የገለጹት አቶ ሙሉጌታ፥ የሽብር ቡድኑ የሀገሪቱ ስጋት እስከማይሆንበት ደረጃ እና ተጎጂዎች ከጉዳታቸው እስኪያገግሙ ድረስ ድጋፉ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
ድጋፉን የተቀበሉት የመቄት ወረዳ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ምላሽ ቡድን መሪ አቶ አታለል ዓለሙ የባለሃብቶቹ ድጋፍ ለሁለተኛ ዙር የተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በወረዳው ከ165 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የገለጹት ቡድን መሪው፥ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገው ድጋፍ ከደረሰው ጉዳት ጋር የሚመጣጠን ባለመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.