Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ባንክ(አባ) አክሲዮን ማኅበር የምስረታ ጉባዔዉን በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡

የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የምስረታ ጉባዔዉን በአዲስ አበባ አካሄደ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የምስረታ ጉባዔዉን በአዲስ አበባ አካሄደ፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕስ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ባንኮች ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል።
በመሆኑም በሀገር ደረጃ ጠንካራ ኢኮኖሚ በመገንባት የብልጽግና ጉዞችንን እናረጋግጣለን ብለዋል ።
ማኅበሩ ከነሐሴ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ 188ሺህ የአክሲዮን እጣ መሸጥ ችሏል፡፡
በዚህም ስምንት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ካፒታል ቃል የተገባ ሲሆን ፤ ሥድስት ቢሊዮን ብር ደግሞ ተሰብስቧል፡፡
አክሲዮን ማኅበሩ 170 ሺህ የአክሲዮን ባለድርሻዎች ያሉት ሲሆን የአክሲዮን ግዢ ስርጭቱም 50 በመቶ በአዲስ አበባ፣ 20 በመቶ በአማራ ክልል እና 30 በመቶ በሌሎች ክልሎች ነው ተብሏል፡፡
የአክሲዮን ማኅበሩ በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ የምሥረታ ጉባዔዉ የሥራ አስፈጻሚዎችን ምርጫ ያካሂዳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.