Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አዲስ ሊቀመንበር መረጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አዲስ ሊቀመንበር መረጠ።

ፓርቲው የካቲት 14 እና 15 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ጉባኤ የአመራር ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል።

አምስት ተለዋጭ አባላት ያሉት 45 የንቅናቄውን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን በሚስጥር ድምፅ አሰጣጥ የመረጠ ሲሆን፥ የተመረጡት አባላትም የድርጅቱን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር መርጠዋል።

በዚህም የፓርቲው ሊቀ መንበር የነበሩት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ከሊቀመንበርነት ተነስተው፥ በለጠ ሞላን (ረዳት ፕሮፌሰር) የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።

ከዚህ ባለፈም አቶ የሱፍ ኢብራሂምን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡንም ነው ፓርቲው ያስታወቀው።

ፓርቲው በጠቅላላ ጉባዔው በተጨማሪም ዘጠኝ አባላት ያሉት በሊቀመንበሩ የቀረቡለትን ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚዎችን አፅድቋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.