Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ለፋሲልና ለባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለቦች ለእያንዳንዳቸው የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ለፋሲልና ለባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለቦች ለእያንዳንዳቸው የ3 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ሀላፊ አቶ አገኘው ተሻገረ የባህር ዳርና ፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ክለቦች በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክልሉን ወክለው የሚጫወቱ በመሆኑ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው እንዲቀጥሉ የገንዘብ ድጋፉ መደረጉን ነው የተናገሩት ።

ሁለቱ ክለቦች የክልሉ መንግስት እያለ በፋይናንስ እጥረት ምክንያት ስራቸው እንደማይቆምም አረጋግጠዋል። በቀጣይ ክለቦቹ የራሣቸው የሆነ የገቢ ምንጭ እንዲኖራቸው መሠራት እንዳለባቸው በማሳሰብ።

ፋሲልና ባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለቦች የክልሉ ፈረጦችና በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጠንካራ ተወዳዳሪዎች መሆናቸው ጠቅሰዋል።

ሁለቱ የእግር ኳስ ክለቦች ዛሬ በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም የመንቀል ዘመቻ ማድረጋቸውን የጠቀሱት አቶ አገኘው፥ ዘመቻው ለሌሎች አራያነት ያለው መሆኑን ገልፀዋል።

 

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.