Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ብድርናቁጠባ ተቋም በ8 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ካፒታል ወደባንክ ሊያድግ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋምበ8 ቢሊዮን ብር ካፒታል አገልግሎቱን ወደ ባንክ ለማሳደግ እየተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ።

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መኮንን የለውምወሰን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ÷ ተቋሙን ወደ ባንክ ለማሳደግ እየተዘጋጀ ያለው ብሔራዊ ባንክ ከሳምንት በፊት ያወጣውን መመሪያ መሰረት በማድረግ መሆኑን ገልጿል።

“የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ወደ ባንክ ልንሸጋገርበት የምንችለውን ዳይሬክቲቭ ወይም ብሄራዊ ባንክ በቁጥር Sbb/74/2020 መመሪያ ሆኖ Augest 15/2020 በብሄራዊ ባንክ ገዥ ተፈርሞ ወጥቷል” ብለዋል።

የመመሪያው መውጣት ተከትሎም በአሁኑ ወቅት ተቋሙ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማቱ ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት ወደ ባንክ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ስያሜውንም “አክሲ” ወይም “አብቁተ” ኢንተርናሽናል ባንክ በሚል እንዲጸድቅለት ለብሄራዊ ባንክ በአማራጭነት ማቅረባቸውን አስረድተዋል።

ከሶስት እስከ ስድስት ወራትም ከ500 የማይክሮ ፋይናንስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ውስጥ በ53ቱ የባንክ አገልግሎቱን ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በአንድ ዓመት ውስጥም በአዲስ አበባና አማራ ክልል በሚገኙ ሁሉም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የተሟላ የባንክ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

ተቋሙ ወደ ባንክ የሚያድገውም 70 በመቶ የክልሉ መንግስት ድርሻ እንደሆነ አመልክተው፤ ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ የግል ባለሃብቶችና ለህብረተሰቡ ሼር በመሸጥ እንደሚሆን ገልጸዋል።

የባንክ ተግባሩን በተሳካ ሁኔታ ለማስጀመርም በ300 ሚሊዮን ብር ወጪ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የ”ዳታ ሴንተር” እና የ”ኮር ባንኪንግ ሲስተም ቴክኖሎጂ ” እየገነባ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የሚዘረጋውን የቴክኖሎጂ ስርዓት ፈጥኖ የሚላመድና ስራውን የሚያቀላጥፍ የሰው ሃይል ለማፍራትም ተከታታይ ስልጠና በመስጠት ተመራጭ የባንክ ተቋም ለማድረግ ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.