Fana: At a Speed of Life!

የአማራ እና የአፋር ክልሎች የፀጥታሥራ ኃላፊዎች የውይይት መድረክ በኮምቦልቻ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ እና የአፋር ክልሎች የፀጥታ ሥራ ኃላፊዎች የሠላምና እና ፀጥታ ውይይት መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
 
የአማራ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው÷መድረኩ የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ታሪካዊና ሁለንተናዊ ትሥሥር እንደሚያጠናክር ታምኖበታል ብለዋል።
 
ሁለቱ ህዝቦች አስተዳደራዊ ወሰን ብቻ ሳይሆን ባሕልና ዕምነት እንዲሁም የደም ትሥሥር ያላቸው ናቸው ያሉት ኃላፊው÷ህዝቦቹ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ መስተጋብር ኖሯቸው በዘመናት የሚገጥማቸውን ችግር ለመፍታት የሚጠቀሙበትም ባሕላዊ መንገድ ውጤታማ ሆኖ የዘለቀ ነው ብለዋል።
 
መድረኩ የክልሎቹን ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ያስችላል የሚል ዕምነት መያዙንም ነው ያመላከቱት ።
 
የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት የሚያጠናክሩ፣ በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል ያሉ መልካም እሴቶችና ተግዳሮቶች፣ በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች የጸጥታ ሁኔታን የተመለከቱ ጽሑፎች በዩኒቨርስቲ ምሁራንና በፀጥታው ዘርፍ አመራሮች ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል።
 
ክልሎቹ ከሰሜን ሸዋ ዞን ጀምሮ እስከ ሰሜን ወሎ ዞን ድረስ የሚዘልቅ አስተዳደራዊ ወሰን የሚጋሩ ህዝቦች ናቸው፡፡
 
በአንድነት ናሁሰናይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.