Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል በግንባታ ላይ የሚገኙ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እንደሚሠራ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በግንባታ ላይ የሚገኙ ከፍተኛ እና መካከለኛ የመስኖ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ የአማራ ክልል መንግሥት በትኩረት እንደሚሠራ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ።

በአማራ ክልል የሚከናወኑ የከፍተኛና መካከለኛ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ያሉበትን ደረጃ ለማወቅና እያጋጠማቸው ያሉትን ችግሮች ለይቶ መፍትሔ  ለመስጠት ያለመ  ውይይት በባህርዳር  እየተካሄደ ነው።

ውይይቱን ያዘጋጀው የክልሉ የከፍተኛና መካከለኛ የመስኖ ፕሮጀክቶች አስተባባሪ ኮሚቴ  መሆኑ ተመላክቷል።

በውይይቱ ላይ የክልሉ ውኃ ፣መስኖ እና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው በክልሉ ሰፊ በመስኖ ሊለማ የሚችል መሬት አለ ብለዋል።

ክልሉ ከፍተኛ የውኃ ሀብት ያለበት መሆኑን ነው የተናገሩት ሃላፊው ÷ ዓባይን ጨምሮ ትልልቅ ወንዞች ያሉበትን የአማራ ክልል ማልማት የዜጎችን ሕይወት በዘላቂነት ለመለወጥ ያስችላልም ነው ያሉት።

በ2002 ዓ.ም ጀምሮ በፌዴራል መንግሥት ድጋፍ ከፍተኛ የመስኖ ፕሮጄክቶች እየተገነቡ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ማማሩ የፕሮጀክቶቹ አፈፃፀም ግን የዘገየ ነው ብለዋል።

በክልሉ እስካሁን ድረስ በመካከለኛ መስኖ ፕሮጀክቶች 103 ሺህ፣ በአነስተኛ እና በባሕላዊ መስኖ ፕሮጀክቶች ደግሞ 280 ሺህ ሔክታር መሬት መልማቱ ተገልጿል።

ሆኖም በመስኖ የለማው መልማት ከሚችለው አንጻር ዝቅተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት።

በመሆኑም ችግሩን ለመፍታት በክልሉ ርእሰ መሥተዳድር የሚመራ አስተባባሪ ኮሚቴ መቋቋሙን ነው የተናገሩት።

አስተባባሪ ኮሚቴውም የከፍተኛ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም በመገምገምና ክትትል በማድረግ ፕሮጀክቶቹ እውን እንዲሆኑ ማድረግ ይገባዋልም ብለዋል።

በመድረኩ በተያዘው በጀት ዓመት የዲዛይን ጥናት የሚጀመርለት የሽንፋ የተቀናጀ የመስኖ ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን አብመድ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.