Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል የመንግስት የልማት ድርጅቶች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት1፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የአማራ ክልል የመንግስት የልማት ድርጅቶችለተፈናቀሉ ወገኖች ከ6 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ እህል ድጋፍ አደረጉ፡፡

የድርጅቱ ድጋፍና ክትትል ተወካይ አቶ መሀመድ ጅብሪል ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት÷ በክልሉ ከሚገኙ 13 መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካሆኑ የልማት ድርጅቶች በተሰበሰበ ገንዘብ ከ1 ነጥብ 6 በላይ የሚገመቱ 250 ኩንታል ዱቄት፣ 3ሺህ ሊትር ዘይትና 90ኩንታል ማካሮኒ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ሀላፊ ለአቶ መሳይ ማሩ በበኩላቸው÷ ተቋማቱ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ በአንድ ላይ ድጋፉን ለተፈናቃይ እንዲደርስ በማድረጋቸው ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ሌሎች ተቋማትም በቅንጅት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከደሴ ከተማ ኮሙዪኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የልማት ድርጅቶቹም በአሸባሪው ህወሓት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በእብናት፣ ባህር ዳር፣ በንፋስ መውጫና፣ ደባርቅ ከተማና በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች በአጠቃላይ ከ6 ሚሊየን 360 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ 1ሺህ ኩንታል ፊኖ ዱቄት፣ 350ኩንታል ማካሮኒና 12ሺህ ሊትር ዘይት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.