Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ለ9ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
በምርቃት መርሃ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡
ርዕስ መስተዳድሩ ዶክተር ይልቃል ከፋለ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ነፃነትና ክብር ያለመስዋትነት አይገኝም ብለዋል፡፡
ጀግንነት በአውደ ግንባር የሚፈጠር ነው ያሉት ዶክተር ይልቃል ÷ተመራቂዎች ለአርበኝነት እና ድል እንዲተጉ የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኮሌጅ ዋና ዳይሬክተር ምክትል ኮሚሽነር አንማው አለሜ÷ ከመከላከያ እና ሌሎች ጸጥታ ሃይሎች ጋር በየአውደ ውጊያው ጠላትን ድባቅ እየመታ የሚገኘው የአማራ ልዩ ሃይልን የተቀላቀሉት ክንደ ነበልባሎቹ የአማራ ልዩ ሃይል አባላት አስፈላጊውን ስልጠና ወስደው መመረቃቸውን ተናግረዋል።
ተመራቂዎች በአውደ ውጊያ ላይ ጀግንነት፣ ዓርበኝነትን እና ተዋጊነትን በተግባር እንዲያሳዩም አደራ ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ በበኩላቸው ÷ ተመራቂ የልዩ ሃይል አባላት ህዝባዊ አደራቸውን በወታደራዊ ስነ ምግባር እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.