Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ ማዕቀብ በኢትዮጵያ ላይ ሊያሳድር በሚችለው  ጫና ላይ የሚመክር ውይይት በድሬዳዋ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን ማእቀብ ተከትሎ ሊያሳድረው በሚችለው ጫና ላይ የሚመክር ውይይት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ኢትዮጵያ እያከናወነችው ባለችው የልማትና የህግ-ማስከበር ስራዎች ብሎም የውስጥ ጉዳዮች ላይ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ማእቀብን ጥሏል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት የአሜሪካ ማእቀብ በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጥረው ተፅእኖ በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ምሁራን በተገኙበት ውይይት አካሂዷል።
በዚሁ ወቅት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሰለሞን ዘሪሁን ÷በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የሚነሱ ሀሳቦች ለሀገር በሚጠቅምና የተሻለ ሀሳቦችን የሚንጸባረቅበት ነው ብለዋል።
በቀጣይም መሰል የውይይት መድረኮች በዩኒቨርሲቲው እንደሚዘጋጅም ዶክተር ሰለሞን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያበርካታ ዩኒቨርሲቲ እንደመኖራቸው እንደዚህ አይነት ማእቀብ ሲጣሉ እንደ ዩኒቨርሲቲ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ምሁራን ለመንግስት ምሁራዊ ሀሳብ የመስጠትና የመደገፍ ሀላፊነት አለባቸው ብለዋል።
ከዚያም ባለፈ ሀገሪቱ ላይ የተከሰተውን ጉዳይ በውጪ ብሎም በሀገር ውስጥ ለሚኖሩ ማህበረሰብ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ የማሳወቁ ሁኔታ ላይ ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ብዙ ስራ ይጠበቃልም ነው ያሉት።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶክተር መገርሳ ቃሲም በበኩላቸው÷እንደዚህ አይነት አጀንዳዎች ላይ መወያየቱ ሊበረታታ እንደሚገባ ሲሉ ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይም ተሳታፊ የሆኑት የዩኒቨርሲቲው መምህራን በበኩላቸው ÷ተማሪዎቻቸው የሀሰት መረጃን እንዳያሰራጩ እንዲጠነቀቁ ማሳወቅ እውነታውንም በተገኘው አጋጣሚ ለአለም ህዝብ ማሳወቅ እንዲገባ ተናግረዋል።
የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብም ሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የውስጥ አንድነታችንን አብሮነታችንን ማስጠበቅ እንደሚገባ መግለጻቸውን ከድሬዳዋ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.