Fana: At a Speed of Life!

የአምባሳደር ስዩም መስፍን ባለቤትና ልጃቸው የ50 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ ፍርድ ቤት ፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአምባሳደር ስዩም መስፍን ባለቤት ፈለገ ህይወት በርሔ እና ልጃቸው አጋዚ ስዩም የ50 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ ፍርድ ቤት ፈቀደ፡፡

ይህ የፈቀደው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በስዩም መስፍን ባለቤት ፈለገህይወት በርሔ እና በልጃቸው አጋዚ ስዩም ላይ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ እና የምርመራ መዝገቡን ይዞ እንዲቀርብ ታዞ የነበረ ሲሆን መርማሪ ፖሊስ ግን መዝገቡን በሌላ መርማሪ ቢሮው ስለተቆለፈ መዝገቡን ይዤ አልቀረብኩም ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ለቀሪ ምርመራ ከኢንሳ የስልክ ልውውጥ መረጃ ለማምጣት ተጨማሪ 14 ቀን የጠየቀ ቢሆንም የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ ግን ይህን ማስረጃ ለማምጣት ብቻ ተጠርጣሪዎችን አስሮ ማቆየት ተገቢነት የለውም ሲል የዋስትና ጥያቄ አንስቷል፡፡

ችሎቱም መርማሪ ፖሊስ ያቀረበው ምክንያት አልተቀበለውም የዋስትና ጥያቄያቸው ተገቢ ነው ሲልም የ50 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ ፍቅዷል፡፡

እንዲሁም ከሀገር እንዳይወጡም እግድ እንዲጣል አዟል፡፡

በታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.