Fana: At a Speed of Life!

የአርሲ ዩኒቨርሲቲና የቀድሞ የደብረብርሃን ተማሪዎች ለተፈናቃዮችና ዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርሲ ዩኒቨርሲቲ እና የቀድሞ የደብረብርሃን ተማሪዎች በሽብር ቡድኑ ህወሓት ወረራ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የትዳር አጋርና ልጆቻቸውን ወደ መከላከያ ሰራዊት ለላኩ ቤተሰቦች ነው 90 ኩንታል ጤፍ ድጋፍ ያደረገው፡፡
 
የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት÷ የትዳር አጋርና ልጅን ወደ አውደ ውጊያ መላክ እራሱን የቻለ የሀገር አለኝታነት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
አገር ሊያዋርድ የተነሳን ሃይል እየደመሰሱ የሚገኙት የጸጥታ አካላት አኩሪ ስራ እየሰሩ ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ለዘማች ቤተሰቦች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
 
የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዱጉማ አዱኛ በበኩላቸው÷ድጋፉ አጋርነትንና አለሁ ባይነትን ለማሳየት የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
በተመሳሳይ የቀድሞ የደብረብርሃን ተማሪዎች ህብረት የበጎ አድራጎት ማህበር ለተፈናቃይ ወገኖች ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የአልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ማህበሩን በመወከል ድጋፉን ያስረከቡት ዶክተር ብሩክ አለሙ÷ የተበረከተው ድጋፍ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ የሚኖሩ የማህበሩ አባላትን በማስተባበር በ15 ቀናት ብቻ የተሰበሰበ ነው ብለዋል።
 
የማህበሩ አባላት በነገው ዕለት ለሃገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ እንደሚያደርጉም ነው ዶክተር ብሩክ የተናገሩት።
 
በሳምራዊት የሥጋት እና ኤርሚያስ ቦጋለ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.