Fana: At a Speed of Life!

የአርበኝነት ንቅናቄው የመላው ጥቁር ሕዝብ መሆን አለበት – ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ላይ ለተከፈተባት ጦርነት የሚያስፈልገው የአርበኝነት ንቅናቄ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ሕዝቦች መሆን እንዳለበት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ተናገሩ።

ቦንጋ ከተማ በተካሄደው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምስረታ በእንግድነት የተገኙት ዶክተር ቢቂላ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለኢዜአ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የውጭ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች ኢትዮጵያ ላይ በቅንጅት የከፈቱትን ጦርነት የእጅ አዙር የቅኝ ግዛት ጦርነት ነው ብለውታል።

ይህ ጦርነት ኢትዮጵያ እንድትወድቅ የሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶቿ የውስጥ ተላላኪዎችን ቀጥረው በተቀናጀ መንገድ የከፈቱት እንደሆነም አንስተዋል።

ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ለመታደግና የጠላቶቻቸውን ጥቃት ለመመከት የአርበኝነት ንቅናቄ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፥ ንቅናቄው ግን የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ሕዝቦች መሆኑን ተናግረዋል።

ዳግም ባርነት እና ቅኝ ግዛትን አንቀበልም የሚሉ መላው ጥቁር ሕዝቦች የኢትዮጵያን የአርበኝነት ንቅናቄ ተቀላቅለው በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ በጋራ እንዲሰለፉም ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያን የሚወድ፣ ባርነትን እና የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝን የሚጸየፍ ሁሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጥሪ ተቀብሎ ወደ ግንባር እንዲዘምትና አገሩንም ቀና እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ዶክተር ቢቂላ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምስረታ የሕዝብ ጥያቄ በሕገ መንግስታዊና በሠላማዊ መንገድ እንደሚፈታ ያመላከተ መሆኑን ገልጸዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.