Fana: At a Speed of Life!

የአርባ ምንጭና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ33ኛ ዙር በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በድህረ ምረቃና በቅድመ መደበኛ መረሃ ግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው፡፡

ተመራቂዎች የሀገሪቱ ብሎም የዓለም የጤና ስጋት ከሆነው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለትህምርት የማይመች ሁኔታን ፈጥሮ ቢሆንም ጥንቃቄ በማድረግና በቴክኖሎጂ በመጠቀም የትምህርት እና የምርምር ሥራቸው ሳይቋረጥ መጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ ተናግረዋል ፡፡

Image may contain: one or more people and indoor

ተቋሙ በልዩ ልዩ የምህንድስና፡ የህክምና፡ የጤና፡ የግብርና፡ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እና በሌሎች የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፎች እስከ አሁን የዛሬዎችን ጨምሮ አጠቃላይ 56 ሺህ 958 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

በተመሳሳይ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 43 ተማሪዎችን ዛሬ አስመረቋል።

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ ያስተማራቸውን ተማሪዎች ሲሆን ያስመረቀው በኪቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተማሪዎቹ የቀሯቸውን ትምህርቶች በኦንላይን ተከታትለው
መጨረሳቸው በምረቃው ላይ ተገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጫና ዋታ በስነ ስርዓቱ ላይ ለተማሪዎቹ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስትላልፈዋል።
ተማሪዎቹ ከኮሮናቫይረስ ራሳቸውን በመጠበቅ ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን የሚጠቅም ስራ እንዲያከናውኑ ጥሪ አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንቱ በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው 17 ሺህ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች ተቀብሎ እያስተማረ ቢሆንም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ግን የመማር ማስተማር መርሃ ግብሩ ተቋርጦ እንደሚገኝ አብረው ጠቁመዋል።

በአስጨናቂ ጉዱና አዳነች አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.