Fana: At a Speed of Life!

በድርድርና ሽምግልና የሚለቀቅ ተጠርጣሪ አይኖርም- ጠ/ዐቃቤ ህግ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በድርድርና ሽምግልና የሚለቀቅ ተጠርጣሪ አይኖርም ሲል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።
 
ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ፍቃዱ ጸጋ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።
 
ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጉ በመግለጫቸው ወንጀልን በሽምግልና የምንፈታበት ህግም ስልጣንም የለንም ነው ያሉት።
 
በአደባባይ ሰው የገደሉና ውድመት እንዲፈጠር ያደረጉ ተጠርጣሪዎች ሳንመረምር አናስርም የሚል የለም ማስረጃውን መዝኖ ለህግ የማቅረብ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
 
በመግለጫቸው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን በመፈጸምና ግድያውን ተከትሎ በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ተብሎ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ክስ እንደሚመሰረት አስታውቀዋል።
 
በሰጡት መግለጫ ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ቀጥታ ተሳትፎ የነበራቸውንና አብራው በነበረችው ግለሰብ ፣ በእነ አቶ ጃዋር መሀመድ መዝገብና በእነ አቶ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይም ክስ እንደሚመሰረት ገልፀዋል።
 
በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ያሉት በአብዛኞቹ ላይ ምርመራው ተጠናቋል ተብሏል።
 
አቶ ፍቃዱ ጸጋ በመግለጫው ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ያለውን አቅም ተጠቅሞ ጥፋተኞችን ለፍትህ የማቅረብ ሂደት በተሻለ ሁኔታ ተፈጻሚ እየሆነ ነው ብለዋል።
 
በኃይለኢየሱስ ስዩም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.