Fana: At a Speed of Life!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ ከነገ ጀምሮ የመጀመሪያውን የመስክ ምልከታ ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ ከነገ ጀምሮ የመጀመሪያውን የመስክ ምልከታ እንደሚያደርግ የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷መርማሪ ቦርዱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
በዚሁ መሠረትም ከነገ ጀምሮ ግጭት ባሉባቸው አካባቢዎችና ልዩ ጥቆማ ባለባቸው አቅጣጫዎች በመንቀሳቀስ የአዋጁን አፈፃፀምና ተይዘው ያሉ ጉዳዮችን ይመለከታል ብለዋል፡፡
ቦርዱ በአዋጁ አፈፃፀም ሂደት ተፈጠሩ ስለሚባሉ የሰብአዊ መብት አያያዝና ጥሰቶች እንዲሁም የሰብዓዊ ዕርዳታ አቀራረብ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራልም ብለዋል፡፡
ከመስክ መልስና በመስክ ወቅትም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በቀጣይ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው የመፍትሔ አቅጣጫዎች ይወያያል፤ ለህብረተሰቡም ግልፅ ያደርጋል ብለዋል፡፡
7 አባላት ያሉት ይኸው ቦርድ የምክር ቤት አባላት፣ የህግ በለሙያዎች እና የፆታ ተዋፅኦን ባከተተ መልኩ የተዋቀረ በመሆኑ÷ የሚያከናውናቸው ማንኛውንም ጉዳዮች ገለልተኛ በሆነ መንገድ ስራዎችን እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ህብረተሰቡ ለሚኖሩት ማንኛውም ጥቆማዎች በነፃ የስልክ ቁጥር 8557 እንዲሁም በስልክ ቁጥር 0111239978 በመደወል ማድረስ እንደሚችልም በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡
በሶዶ ለማ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.