Fana: At a Speed of Life!

የአስገንጣዩ ቡድን መሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ካታሎን ከእስፔን እንድትገነጠል ጫና ሲያደርግ የነበረዉ ቡድን መሪ ካርለስ ፔጅሞንት በጣሊያን በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
የካታሎኒያ ግዛት ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረዉ ሚስተር ፔጅሞንት በ2017 ካታሎኒያ ከእስፔን እንድትገነጠል የሚፈልገዉን የፖለቲካ ቡድን ሲመራ ቆይቷል፡፡
ይሁን እንጅ በተደረገዉ ህዝበ ዉሳኔ ምርጫ ካታሎን ከእሰፔን ሳትገነጠል ቀርታለች፡፡
የምርጫዉን ዉጤት ተከትሎም ፔጅሞንት ከእስፔን በሙዉጣት ኑሮዉን በቤልጂየም አድርጎ ቆይቷል ነዉ የተባለዉ፡፡
ግለሰቡ በሃገሪቱ በተፈጠረዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት የስፔን መንግስት ክስ መስርቶበት ነበር ተብሏል፡፡
ለዓመታት ተሰውሮ የቆየው ግለሰቡ÷ የካታሎንን ፌስቲቫል ለመታደም በረራ ላይ በነበረበት ወቅት በዛሬዉ እለት በጣሊያን ፖሊሶች በቁጥጥር ስር መዋሉን ሮይተረስ በዘገባዉ አስታዉቋል፡፡
በዚህ ሳምንትም ግለሰቡ ወደ ፍረድ ቤት እንደሚቀርብ ጠበቃዉ አስታዉቋል፡፡
በካታሎንና በሰፔን መካከል በነበረዉ የፖለቲካ ዉጥረት ከ2017 ጀምሮ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን÷ ሪፈረንደም ተደረጎ ካታሎን በማድሪድ ህጎች እንድትመራ መደረጉ የሚታወስ ነዉ፡፡
ምንጭ፡- ሮይተርስ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.