Fana: At a Speed of Life!

የአሸባሪውን ቀብር በወሎ ምድር ላይ እናደርጋለን- ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ወሎ የዘመቱ ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2014 (አኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪውን ህወሓት ወራሪ ኃይል ሙሉ ለሙሉ ደምስሰን የመጨረሻ ቀብሩን በወሎ ምድር እናደርጋለን ሲሉ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ወደ ወሎ ግንባር የዘመቱ ወጣቶች ገለጹ፡፡
ከጎንደር ከተማ የመጣው ወጣት ሙላት አድነው ለኢዜአ እንደገለጸው÷ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከውጭና ከውስጥ ባንዳዎች ጋር ወግኖ እየሰራ ያለውን የአሸባሪውን ህወሀት ቡድን ተባብሮ መቅበር ሀገራዊ ሀላፊነት ነው።
ቡድኑ ሰርጎ በገባባቸው የአማራና አፋር አካባቢዎች በንጹሀን ላይ ዘግናኝ ግፎችን መፈጸሙን አስታውሶ፤ በጠንካራ ክንዳችን የቡድኑን የመጨረሻ ቀብር ወሎ ላይ እናደርጋለን ብሏል።
እንደ ጀግኖች አባቶቻችን መስዋዕት ከፍለን ኢትዮጵያን ከጥፋት ቡድኑ ነጻ እናወጣለን ብሏል።
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምጣቱን የገለጸው ወጣት ኢንጂነር ይበልጣል ታደሰ በበኩሉ እንደገለጸው÷ የሀገር ነቀርሳ የሆነው የሽብር ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ ካልጠፋ ህዝብ በሰላም አይኖርም።
የጥፋት ቡድኑ በፈጸመው ዘግናኝና አስነዋሪ ግፍ ወገኖቻችን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው፣ በጅምላ ተገድለውና ተዘርፈው አዲስ አበባ መቀመጥ አልቻልኩም ሲልም ወጣቱ ተናግሯል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.