Fana: At a Speed of Life!

የአንበጣ መንጋ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት –  ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአንበጣ መንጋ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

8ኛው የተፋሰሶች ከፍተኛ ምክር ቤት ጉባኤ በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን፥ ጉባኤው የጎርፍ፣ አንበጣ እና እምቦጭ አረም በደቀኑት አደጋ ላይ በስፋት መክሯል፡፡

በጉባዔው ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዳሉት ፥ በኢትዮጵያ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ በተለይ በደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ውድመት እያስከተለ ይገኛል።

በዚህም የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል መንግስት የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰው፤ ኬሚካል የሚረጩ አውሮፕላኖችን ከውጭ አገር ለማስገባት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

መንግስት የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ባለድርሻ አካላት እንዲደግፉም የጠየቁ ሲሆን÷በእስካሁኑ ሂደት ማህበረሰቡ አንበጣውን ለመከላከል በየአካባቢው ያደረገውን ጥረት አድንቀዋል።

በሃይለየሱስ መኮንን

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.