Fana: At a Speed of Life!

የአንድ ወር የእምቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጥቅምት 9 እስከ ኅዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆየው የእምቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
በዘመቻው ጣና ሐይቅን የወረረው የእምቦጭ አረም በተቻለ መጠንና በዘላቂነት እንደሚወገድ ይጠበቃል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በዚህ ንቅናቄ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ዘመቻውን ያስጀመሩ ሲሆን የውሃ አካላት የሚያስገኙት ውጤት በሚደረገው እንክብካቤ ላይ የተወሰነ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ሀገሪቱ ካላት ውስን ምጣኔ ሀብት አንፃር ለሁሉም የውሃ አካላት እንክብካቤ ማድረግ እንዳልተቻለም ነው ያነሱት፡፡
የዚህ ችግር ሰለባ የሆነውን ጣና ሀይቅ ለመታደግ በተለያየ ጊዜ ጥረት መደረጉን የገለፁት ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ወደ ኋላ ባለማፈግፈግ መጤ አረሙን ለማስወገድ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል።
እንቦጭን ለማጥፋት በጊዚያዊነት ከተጀመረው ዘመቻ ባለፈ በቋሚነት የሃይቁን ዳርቻዎች በቋሚ ተክሎች መተካት፣ የአፈርና የውሃ ጥበቃ ስራዎችን መስራት፣ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠርና መሰል መፍትሔዎች መዘጋጀታቸውንም አስረድተዋል።
ዘመቻው ውጤታማ እንዲሆንም ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ተጠይቋል።
በሳራ መኮንን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.