Fana: At a Speed of Life!

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስፖርት በሁሉም ስፍራ እንዲደርስ እየተሰራ ነው  – የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስፖርት በሁሉም ስፍራ ደርሶ አብሮነትን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ከሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር “አብሮነታችን ለሀገራችን “በሚል መሪ  ሀሳብ ዛሬ በደብር ብርሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄዷል።

የኢፌዴሪ ስፖርት  ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር በወቅቱ እንዳሉት፤ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለአካል መጠንከርና አእምሮ እድገት ወሳኝ ነው።

ሚዛናዊ አስተሳሰብ ኖሮ የሀገሪቱ ሠላም እንዲጠበቅ የተጀመረው የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸው፤ አብሮነትን በማጠናከር እኩልነትና መተሳሰብ በህዝቦች መካከል እንዲሰርፅ ያግዛል ብለዋል።

መንግስትም ስፖርት ለሁሉም በሁሉም ስፍራ እንዲደርስ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽነር አቶ ባዘዘው ጫኔ በበኩላቸው፤ የተጀመረው የጋራ ሥራ በአዲስ አበባ እና አማራ ህዝብ መካከል መተሳሰብንና መቀራረብን ያጠናክራል ብለዋል።

በክልሉ በሚገኙ ከተሞችና ወረዳዎች ከነገ ጀምሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚካሄድ ጠቁመው÷ ሁሉም ህብረተሰብ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ  ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽነር አቶ በላይ ደጀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመቅረጽ ጠቀሜታው የጎላ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በቅርበት በሚገኙ ከተሞች ተዘዋውሮ በማካሄድ የዜጎችን የአብሮነት እሴት ለማሳደግ ይሰራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.