Fana: At a Speed of Life!

የአዊ ልማት ማኅበር በአዲስ አበባ ለሚያስገነባው ሁለገብ ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የአዊ ልማት ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚያስገነባው የባህል ማዕከል እና ሁለገብ ሕንፃ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን በዚሁ መርሐ-ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የአዊ ሕዝብ ማኅበራዊ ትውፊቶች እና መስተጋብሮች ያሉት የበርካታ ታሪክ እና ቅርስ ባለቤት ነው ብለዋል።

ባህላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶችን ለማሳየት ሁለገብ ሕንፃው አዲስ አበባ ላይ መገንባቱ ፋይዳው ትልቅ ነው ያሉት አቶ ደመቀ፣ “ትውልድ ተሻጋሪ እና አኩሪ ታሪክ ለመሥራት ቃልን በተግባር መፈፀም ይገባል” ሲሉም ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር ዓባይ በበኩላቸው፥ የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን መሆኗን ለማሳየት ትላልቅ ሥራዎች እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

ማዕከሉ አዲስ አበባ ውስጥ መገንባቱ ወደ አካባቢው ተጉዘው መጎብኘት ለማይችሉ ቱሪስቶች የቱሪስት መስህብ ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል።

የባህል ማዕከል እና ሁለገብ ሕንፃው 15 ወለሎች ያሉት ሲሆን፥ 1ሺህ 700 ካሬ ሜትር መሬት ላይ እንደሚያርፍ ተገልጿል ሲል የዘገበው ኢቢሲ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.