Fana: At a Speed of Life!

የአዋሽ ወንዝ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ተጎጂዎች ለውሃ ወለድ በሽታ እንዳይጋለጡ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 3 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዋሽ ወንዝ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ተጎጂዎች ለውሃ ወለድ በሽታ እንዳይጋለጡ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ያሲን ሀቢብ እንደገለጹት ÷ ተጎጂዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች በተንቀሳቃሸ ክሊኒክ የህክምና ቡድን ተሰማርቶ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

በወባ በሽታ በዘንድሮ አመት በክልሉ 100 ሺህ 92 ሰዎች መታመማቸውን ያስታወሱት ሃላፊው÷አሁንም የጎርፍ ውሃው ክምችት ከሞቱ እንስሳት ብክለት ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችል የወባ እና የኮሌራ በሽታን ቀድሞ ለመከላከል በጥናት ተለይቶ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአፋር ህብረተሰብ ጤናና  ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር  አቶ ሐመዱ አህመድ በበኩላቸው÷ በመደበኛነት ይሰራጭ የነበረው የመኝታ  አጎበር ከወረዳዎች ጋር በመሆን ተጎጂዎች ባሉበት ስፍራ ስርጭቱ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ሃላፊው አያይዘውም በአደጋው የተፈናቀሉ ሰዎችን ጤና ለመጠበቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ  ይሆናል ብለዋል።

በመለሰ ምትኩ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.