Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ከአሜሪካ፣ ብራዚል እና ሩሲያ ለሚመጡ መንገደኞች በሩን ዝግ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ከአሜሪካ፣ ብራዚል እና ሩሲያ ለሚመጡ መንገደኞች በሩን ዝግ ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ።

የህብረቱ አባል ሃገራት ከመጭው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ ድንበሮቻቸውን ከከፈቱ በኋላ ከሌሎች ሃገራት በሚመጡ መንገደኞች በአባል ሃገራቱ በሚኖራቸው የጉዞ እንቅስቃሴ ላይ ለመወሰን ትናንት ተሰብስበው ነበር።

በስብሰባቸውም አባል ሃገራቱ ከፈረንጆቹ ሃምሌ 1 ጀምሮ ድንበሮቻቸውን ሲከፍቱ ያለ ለይቶ ማቆያ ወደየሃገራቱ መግባት የሚፈቀድላቸውን የሃገራት መንገደኞችን ጊዜያዊ ዝርዝር አውጥተዋል።

ዝርዝሩ ከ18 ሃገራት የሚመጡ መንገደኞች ወደ ህብረቱ አባል ሃገራት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲገቡ ጊዜያዊ ይሁንታን መስጠቱ ተገልጿል።

በዚህ ዝርዝር ውስጥ ከአሜሪካ፣ ብራዚል እና ሩሲያ የሚነሱ መንገደኞች ግን በሃገራቱ ካለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያያዘ ወደ አባል ሃገራቱ እንዳይገቡ ይደረጋል ነው የተባለው።

አሁን ላይ በጊዜያዊነት በቀረበው ዝርዝር ላይም የየአባል ሃገራቱ መሪዎች የመጨረሻ ውሳኔያቸውን ዛሬ ያሳውቃሉ ተብሏል።

በአንጻሩ ከቻይና የሚመጡ መንገደኞች ቤጂንግ ለአውሮፓውያኑ በተመሳሳይ በሯን ክፍት ካደረገች መግባት እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።

ምንጭ፡- አልጀዚራ እና ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.