Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ኅብረት እና አሜሪካ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያቀርቡት የመፍትሄ ሃሳብ ፖለቲካዊ ፍላጎታቸውን እንጂ እውነታውን ያገናዘበ አይደለም – ዶክተር ቤንጃሚን ኡጁማዱ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይጄሪያ የዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ተንታኝ ዶክተር ቤንጃሚን ኡጁማዱ በኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ላይ የአውሮፓ ኅብረት እና አሜሪካ አሳፋሪ ሰነዶችን ሲያቀርቡ መቆየታቸውን አመላክቷል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ሰነድ በአሸባሪው ህወሓት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን፣ ጭፍጨፋዎችን እና ውድመቶችን ከግንዛቤ ሳያስገባ የፓርላማ አባላቱን በማወያየት ብቻ ፖለቲካዊ ፍላጎታቸው ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሳልፏል ብሏል፡፡

ዶክተር ኡጁማዱ፥ ኅብረቱ በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያሳሰበው ቢመስልም እውነታው ግን በአሸባሪው ህወሓት ቡድን ምክንያት በአፋርና በአማራ ክልሎች የደረሰውን ሰቆቃ፣ የጅምላ መፈናቀል፣ የምግብ አቅርቦት ችግር ፣ እና ሽብር በሰነዱ ሳይዳስስ በትግራይ ክልል ደረሰ በሚለው ረሃብ ላይ ብቻ ማተኮር መምረጡ ነው ብሏል፡፡

አሜሪካ በሌላ በኩል ህገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ በህዝብ ለተመረጠው መንግስት እውቅና በመንፈግ ከአሸባሪው የህወሓት ቡድን ጋር ተባብራለች ሲሉም ዶክተር ኡጁማዱ ያብራራሉ፡፡

የአሜሪካ መንግስት ዲፕሎማቶቹ እና ዜጎቹ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ በተደጋጋሚ ሲያሳስብ መቆየቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀውስ እና አለመረጋጋት እንደሰፈነ ብሎም ሀገሪቷ በአሸባሪ ቡድኑ ቁጥጥር ስር እንደምትወድቅ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በመንገር ትኩረት ለመሳብና በፖለቲካዊ ፕሮፖጋንዳው ጣልቃ ገብቶ የኢትዮጵያን እጅ በመጠምዘዝ በድርድር ጉዳይ አስፈጻሚውን አሸባሪ የህወሓት ቡድን ለማዳን ያለውን ፍላጎት ያንጸባረቀ እንደሆነም ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ተንታኙ አመላክቷል፡፡

ጸሃፊው፥ የአውሮፓ ኅብረትም ሆነ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው ፍላጎት ታዛዥ መንግስት በማስቀመጥ በእጅ አዙር ቅኝ መግዛት እንደሆነም አስምሮበታል፡፡

አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ወደ ሥልጣን ለመመለስም በዘመናዊ የራዳር መገናኛ ዘዴዎች ጭምር ሲደግፉት ነበር ብሏል፡፡

ፀሐፊው ÷ አሜሪካ እና አውሮፓ የምግብ እርዳታ አቅርቦት፣ የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ የተባረሩ የኅብረቱን ሠራተኞች ጉዳይ፣ በኢትጵያ በሚኖሩ ዜጎቻቸው እና ዲፕሎማቶቻቸው ደህንነት ላይ፣ በትግራይ የሚፈጸሙ በደሎች፣ እና የተለያዩ አጀንዳዎችን እያነሱ ጣልቃ በመግባት በአሸባሪ ቡድኑና በኢትጵያ መንግስት መካከል የተፈጠረውን ጦርነት መቋጫ እንዳያገኝ ማድረጋቸውን ዘ ጋርዲያን ላይ አስነብቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.