Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ የቀውስ ሥራ አመራር ኮሚሽነር መንግስት የሰሜን ኢትዮጵያን የሰላም ሁኔታ ለማሻሻል እያደረገ ያለውን ጥረት አደነቁ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 8፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የአውሮፓ የቀውስ ሥራ አመራር ኮሚሽነር ጄኔዝ ሌናርሲች መንግስት የሰሜን ኢትዮጵያን የሰላም ሁኔታ ለማሻሻል እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ከአውሮፓ ቀውስ ሥራ አመራር ኮሚሽነር ጄኔዝ ሌናርሲች ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና በሌሎች የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ በቤልጂየም ብራስልስ ከተማ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸውም÷ በሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ እየተደረገ ስሚገኘው ጥረት እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስት ግጭትን ለማስቆም በሚወስዳቸው የሰላም እርምጃዎች ጋር በተያያዘ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

ኮሚሽነሩ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን የሰላም ሁኔታ ለማሻሻል በመንግስት በኩል እየተደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው፥ አሁን ያለውን መነቃቃት በማጎልበት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገበውን እድገት የበለጠ ለማጠናከር ሁለቱ ወገኖች ተቀራርበው ለመስራት መስማማታቸውም ተገልጿል።

ዶክተር ጌዲዮን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከተለያዩ የአውሮፓ ህብረት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቀጣዮቹ ቀናት ውይይት ለማድረግ ብራስልስ መግባታቸውን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.