Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ ሌሎች የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ ሌሎች የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት  እንዲቀጥል  መወሰኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

መንግስት የሀገሪቱ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ ሌሎች  የነዳጅ ምርቶች አሁን በስራ ላይ ባለው የመሸጫ ዋጋ እንዲቀጥል  መወሰኑ ተገልጿል።

በዚህም  ከሚያዚያ 29 እስከ ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም  ድረስ  አሁን በስራ ላይ ያለው የመሸጫ ዋጋ የሚቀጥል ሲሆን÷ በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደርግ የሚችል መሆኑን ከንግድና  ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.