Fana: At a Speed of Life!

የአውስትራሊያ ሰደድ እሳት ጭስ የኒውዝላንድን ሰማይ ባልተለመደ ሁኔታ ቀይሮታል

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 23፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የአውስትራሊያ ሰደድ እሳት ጭስ የኒውዝላንድን ሰማይን ባልተለመደ ሁኔታ ቢጫ ማድረጉ  ተነግሯል፡፡

ከአውስትራሊያ ሰደድ እሳት  የሚነሳው ጭስ 1 ሺህ 200 ማይሎች  ርቆ ወደ ኒው ዚላንድ በመሰራጨት አካባቢውን ጭጋጋማ ከማድረጉ በላይ የቃጠሎ ሽታ መሽተት መጀመ ተገልጿል፡፡

ጭሱ መጀመሪያ በፈረንጆቹ  ታህሳስ 31 ቀን በኒውዚላንድ ደቡብ ደሴት አካባቢ  አቧራማ ቢጫ  ቀለም ይዞ መታየቱ ተነግሯል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በኒውዝላንድ ደቡብ ታዋቂው የበረዶ ግግር  መቅለጡና እና የሰሜን ደሴት  ሰማይም  ወደ አቧራማ  ቀለም ተቀይሯል፡፡

ቱሪስቶች የኒው ዝላንድን  አስገራሚ የተራራማ አካባቢዎች ለመጎብኘት ወደ ታዝማን ፣ ፍራንዝ ጆሴፍ እና ፎክስ የበረዶ ግግር  ያቀናሉ።

ነገር ግን ከቅርብ ቀናት ወዲህ  ከሚጠበቁት ነጭ በረዶ እና ደማቅ ሰማያዊ ሰማዮች ይልቅ ወፍራም ቢጫ ጨረር በአካባቢው እንደሚያዩ ነው የተነገረው፡፡

በተለይ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ  የተቃጠለ የእንጨት ሽታ ሲሸት ነበር ብለዋል፡፡

የአውስትራሊያ የጫካ ሰደድ እሳት ቀውስ በከፍተኛ ሙቀትና በወራት በዘለቀው ድርቅ ምክንያት እየተባባሰ መምጣቱ ተነግሯል፡፡

በደቡባዊ አውስትራሊያ የተከሰተው ሰደድ እሳት አድማሱን በማስፋት እስካሁን ለ8 ሰዎች ህልፈት ምክንያት ሲሆን፥

ከ200 በላይ ቤቶች መውደማቸውም ተሰምቷል።

 

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.