Fana: At a Speed of Life!

የአይሻ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወደ ግንባታ ማሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶማሌ ክልል ሊገነባ እቅድ ተይዞለት የነበረውን የአይሻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታን አስመልክቶ ፕሮጀክቱን ወደ ግንባታ መሸጋገር በሚችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር ተካሂዷል፡፡
ምክክሩ የተካሄደው የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ የክልልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እንዲሁም ሌሎች የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ነው፡፡
በመድረኩም የፓርኩን ግንባታ አስመልክቶ የተከናወኑ የሳይት መረጣ ዳሰሳ እና የከርሰ ምድር ውሀ ጥናት ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በቀጣይ 20 አመታት በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች እንዲገነቡ በስፓሻል ጥናት ከለያቸውና በዘርፉ እምቅ አቅም አላቸው ተብለው በተለዩት አካባቢዎች ከሚገነቡ ከ100 በላይ የኢንዱስተሪ ፓርኮች መካከል ሰባት ያህሉ በሶማሌ ክልል እንደሚገኙ መጠቆሙን ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያል ዴቨሎፕመንት ኮርፖሬሽን ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.