Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በትግራይ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ ችግሮች ለተፈናቀሉ ወገኖች 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በትግራይ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ ችግሮች ለተፈናቀሉ ወገኖች የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በተከሰተው ወቅታዊ ችግር ጉዳት ለደረሰባቸው እርዳታ እና ድጋፍ እንዲደረግ በወሰነው መሠረት ነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረገው፡፡
ይህን በሚመለከትም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
በመግጫው የአዲስአበባ እና የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ለጉዳዮ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን የኒውዮርክ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በበኩላቸው በትግራይ ክልል ጉብኝት በማድረግ የችግሩን መጠን እንደተመለከቱ ገልጸው ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉት አህጉረ ስብከቶች እርዳታ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድዖ ኮሚሽን በትግራይ እና ቤኒሻንጉል ክልል ለሚከናወን ሰብአዊ ድጋፍ የ 81ሚሊየን ብር ፕሮጀክት ቀርፆ እየሠራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ÷ከዚህ ውስጥ 35 ሚሊየን 940 ሺህ ብር የፋይናንስ ድጋፍ ተገኝቶ ተግባራዊ ሥራ መጀመሩን ኮሚሽነሩ አቶ ይልቃል ሽፈራው ገልጸዋል፡፡
በዚህም በራያ ወረዳ ለ6 ሺህ 500 ችግረኛ ወገኖችን የቤት ቁሳቁስ እየታደለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድዖ ኮሚሽን በመቐለ በመጸዳጃ ቤት እና ዉሃ አቅርቦት እየሠራ እንደሆነ መገለፁን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ስርጭት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.