Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ስታዲየም የዕድሳት ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ስታዲየም የዕድሳት ስራ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።
የአዲስ አበባ ስታዲየምን እድሳት ለማድረግ ከሁለት ሳምንት በፊት የውል ስምምነት መደረጉ ይታወሳል።
በውሉ መሠረትም የእድሳት ስራው ዛሬ ተጀምሯል።
ዕድሳቱ በቅድሚያ ካፍ የሰጣቸውን አስተያየቶች መሠረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን፥ የመጫወቻ ሜዳው ፣ የመልበሻና የመታጠቢያ ክፍሎች ፣ የተመልካች መፀዳጃ እና የኤሌክትሪክ እና የጽዳት ስራዎችን የሚያካትት ይሆናል።
የእድሳት ስራውን ፍሬንድስ ኢንጅነሪንግ አማካኝነት እንደሚሰራ ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.