Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የማህበር ቤት ፈላጊዎችን ምዝገባ ሊያካሂድ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የማህበር ቤት ፈላጊዎችን ምዝገባ ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ፡፡
በምዝገባው ተጠቃሚ የሚሆኑት በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት መርሐ ግብር ተመዝግበው ቤት ለማግኘት የሚጠባበቁት ናቸው ተብሏል።
ምዝገባውን በኦንላይን እንደሚከናወን ቢሮው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
በመግለጫው ከቀጣዩ ሣምንት ጀምሮ የመገንባት ፍላጎት እና አቅም ያላቸውን ነባር የቤት ፈላጊዎች በኦንላይን የመመዝገብ ስራ እንደሚጀመር እና በምዝገባው የሚካተቱት በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና 40 /60 የቤት ልማት ፕሮግራሞች ተጠቃሚ ለመሆን የተመዘገቡ ፣ስማቸው በምዝገባ ቋት የሚገኝ እና የቁጠባ ደብተር ሂሳብ ያልዘጉ መሆን እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ዶክተር መስከረም ዘውዴ አብራርተዋል ።
በተጨማሪም በማህበር ቤት ለመገንባት ተመዝግቦ ዕጣ የወጣለት ተመዝጋቢ የግንባታውን ወጪ70 በመቶ በሚመረጥ ባንክ በዝግ ማስቀመጥ ይኖርበታል ብለዋል ።
ተጠቃሚው በአዲስ አበባ በራሱም ሆነ በትዳር አጋሩ ስም ቤት ወይም የቤት መስሪያ ቦታ የሌለው፤ ወይንም የነበረውን ከ1997 ዓ.ም ወዲህ በስጦታና በሽያጭ ለሶስተኛ ወገን ያላስተላለፈ መሆን እንዳለበት በመግለጫው ተጠቅሷል ።
በግንባታው የከተማዋ ማስተር ፕላን በሚፈቅደው ከባለ አራት ፎቅ እስከ ባለ 15 ፎቅ ህንጻ ድረስ እንደሚገነባ እና በመጀመሪያው ዙር ከ10 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ተጠቁሟል ።
መስፈርቱን የሚያሟሉ ነባር የ20/80 እና የ40/60 የማህበር ቤት ፈላጊዎች ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ምዝገባውን aahdab.gov.et በሚለው የቢሮው አድራሻ በኦንላይን መመዝገብ እንደሚችሉ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.