Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 6ሺህ 891 ተማሪዎች አስመረቀ ።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ ተገኝተዋል።

በዛሬው እለት የተመረቁት 6 ሺህ 891 ተማሪዎች የ2012 ዓ.ም ተመራቂዎች ሲሆኑ በ2013 ዓ.ም የወሰዱትን የማካካሻ ስልጠና ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ ”ዘርፉ አገራችን ለተያያዘችው ግስጋሴና አገር በቀል በሆነው የኢኮኖሚ ሪፎርም ውስጥ ትልቅ ሚና አለው”።

”ወጣትነት ማለት ሁሉን ለማድረግ የሚቻልበት ጊዜ በመሆኑ በተሰጣችሁ ጊዜ በዘርፉ የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት መስራት ይገባችኋል” በማለት ከዚህ ቀደም ”በጠቅላይ ሚኒስትሩ ”ስለወጣቶች አቅም የተባለውን ለተመራቂዎች ማጋራታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው ዘርፉ አገሪቷ ከድህነት ለመውጣት በምታደርገው ጥረት ውስጥ ድርሻው የላቀ እንደሆነ አንስተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.