Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ61 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የከተማ አስተዳደሩን የ2013 በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ61 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የከተማ አስተዳደሩን የ2013 በጀት አጽድቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የ2013 በጀት ዓመት እና ልዩ ልዩ ሹመት በማጽደቅ ተጠናቋል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው ከተመለከተው ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2013 በጀት አንዱ ነው።

በዚህም ምክር ቤቱ ለ2013 በጀት ዓመት ለካፒታል እና ለመደበኛ ስራ ማስኬጃ 61 ቢሊየን ብር በጀት ሆኖ የቀረበለትን በጀት አጽድቋል።

ከዚህ በተጨማሪም ምክር ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር  ታከለ ኡማ የቀረበለትን የሁለት ቢሮ ሃላፊዎችን ሹመትንም ተቀብሎ አጽድቋል።

በዚህ መሰረት፦

  1. ወይዘሪት ፋይዛ መሐመድ – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል ቱሪዝም እና ኪነጥበብ ቢሮ ኃላፊ
  2. ወይዘሪት ሓዳስ ኪዱ – የሴቶች እና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል

አዲሶቹ ተሿሚዎችም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.