Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት ከ70 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ70 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሰንጋዎች፣ እሽግ ውሀዎች፣ የደረቅ ምግቦችና የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለመከላከያ ሠራዊት በወሎና በሃርቡ ግንባር በመገኘት ድጋፍ አድርጓል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት “የአሸናፊነት የምድር ድሮኖች” መሆናቸውን ገልጸው፥ የህወሓት የሽብር ቡድንን ለመደምሰስ አይነተኛ ሚና መጫወታቸውን ገልጸዋል።

ለመከላከያ ሠራዊቱ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያነሱት።

የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ዋና አዛዝ ሜጀር ጀነራል ሹማ አብደታ በበኩላቸው የልዩ ኮማንዶዎች ሪፐብሊካን ጋርድ የህወሓት የሽብር ቡድንን በመደምሰስ በኩል የማይተካ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.