Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአማራ ክልል ተፈናቃዮች ከ385 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአማራ ክልል በህወሓት ወረራ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል ከ385 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ከተደረገው አጠቃላይ ድጋፍ ውስጥም 350 ሚሊየኑ በጥሬ ገንዘብ የተበረከተ ሲሆን ÷ 35 ሚሊየን 134 ሺህ 128 የሚሆነው ደግሞ የአይነት ድጋፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር አስረክበዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የተመራ የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ባሕር ዳር መግባቱ ይታወሳል፡፡

በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.