Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለዋልያዎቹ 5 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ማበረታቻ ሽልማት አበረከተ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ33ኛ አፍሪካ ዋንጫ ላለፈው የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን (ዋልያዎቹ) 5 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ማበረታቻ ሽልማት አበረከተ።

አስተዳደሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ላስመዘገበው ውጤት እጅግ የላቀ ክብርና አድናቆት እንዳለው ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ ገልፀዋል።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለቡድኑ አባላት በጥረታችሁ ታሪክ ለማስመዝገብ በመብቃታቹህ፤ ለሃገራችሁ የተለየ የመነቃቃት ስሜት ፈጥራችኋል ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም ለብሄራዊ ቡድኑ እና ለአጠቃላይ የስፖርቱ እድገት ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.