Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ በ28 ሺህ በላይ ሴቶች እና ወጣቶችን ወደ ስራ አሰማራ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ በ28 ሺህ በላይ ሴቶች እና ወጣቶችን ወደ ስራ አሰማራ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ28 ሺህ በላይ ሴቶች እና ወጣቶች አዲስ የስራ እድል ለመፍጠር ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሁሉም የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልጿል፡፡

ስልጠናው ሲሰጥ የቆየው በተቀናጀ የከተማ ውበት፣ አረንጓዴ ልማት እና በደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ እንዲሁም በሌሎች የስራ ዘርፎች ነው፡፡

በዛሬው ዕለትም ስልጠና ሲውስዱ የነበሩ ሴቶች እና ወጣቶች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ወደ ስራ ተሰማርተዋል፡፡

በትዝታ ደሳለኝ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.