የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 3ኛውን የምገባ ማዕከል አስጀመረ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 3ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስጀመረ።
በምገባ ማዕከሉ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና የዳሽን ባንክ ተወካይ አመራሮች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግርም÷ ማዕከሉ ከምገባ ማዕከልነቱም ባሻገር በቀጣይ ዜጎች በማዕከሉ የተለያዩ ስልጠናዎችን አግኝተው የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል ብለዋል።
ይህ ማዕከል በቀን 2ሺ ለሚሆኑ ዜጎች በቀን አንድ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጥ ማእከል መሆኑ ተገልጿል።
ከተማ አስተዳደሩ ባለሀብቶችና አጋር አካላትን በማስተባበር በከተማ አስተዳደሩ 5 ክፍለ ከተሞች ላይ የተስፋ ብርሀን የምገባ ማእከል ለማስጀመር እቅድ ይዞ ነበር።
በዚህ እቅድ መሰረት በመጀመሪያው እና በሁለተኛው ዙር በአራዳ እና በቦሌ ክፍለከተሞች ላይ የምገባ ማዕከል ማስጀመሩ ይታወሳል።
በዛሬው እለትም ከሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር ነው 3ኛውን የተስፋ ብርሃን አሙዲን የምገባ ማዕከል ያስጀመረው።
በትዝታ ደሳለኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!