Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ሰባት ወራት 24 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ሰባት ወራት 24 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አስታውቋል።

ቢሮው በቀጣይ በሚያደርገው የገቢ ማሻሻያ የታክስ ንቅናቄ መሪ እቅድ ዙሪያ
ከሚመለከታችው የመንግስት አካላትና የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር እየመከረ ነው።

በዚህ ወቅት ባለፉት 7 ወራት 25 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 24 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልጿል።

የተሰበሰበው የግብር ገቢ የዕቅዱን 95 በመቶ መሆኑንም ነው ቢሮው የገለጸው።

ገቢው ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተመላክቷል።

በተስፋዬ ከበደ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.