Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን እና ጃይካ የ490 ሺህ ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ከጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ጃይካ) ጋር የ490 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ስምምነት ተፈራረመ፡፡
 
ፕሮጀክቱ ከ51 ሺህ በላይ ደንበኞችን ያቀፈ ሲሆን÷ በንፋስ ስልክ እና መካኒሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ላይ የሚተገበር መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
በአሁኑ ሰዓትም ከተጠቀሱት አካባቢዎች መረጃ በመሰብሰብ እና የተመረጡት ቅርንጫፎች ወቅታዊ የሆነ መሰረተ ልማቶችን ካርታ ላይ የማስፈር ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ በባለሥልጣኑ ገቢ የማይሰበሰብበት ውሃ ክትትልና ቁጥጥር ባለሙያ አቶ ሃብታሙ ታደሰ ገልጸዋል፡፡
 
በቀጣይም ድርጅቱ በተመረጡት ቅርንጫፎች ከተሰራጨው ውሃ ምን ያህሉ ጥቅም ላይ ይውላል? ምንስ ያህሉ ይባክናል? የት አካባቢ? የሚለውን በመለየት አስፈላጊውን የስርጭት ማስተካከያ እንደሚያደርግ አብራርተዋል፡፡
 
ስራው የሚባክን ውሃ ከመቀነስ ባለፈ ለስርጭት ባለሙያዎች ክህሎትን ለማዳበር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት መገለጹን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ፕሮጀክቱ ለአራት አመት የሚቆይ ሲሆን፥ ለስራ የሚያስፈልጉ ማንኛውም ግብዓቶች በጃፓን ዓለም አቀፍ ድርጅት ጃይካ የሚሸፈን ይሆናል ፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.