Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ12 ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ12 ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሚሰጣቸው ምሁራን በመማር ማስተማሩ፣ በጥናትና ምርምር፣ በዩኒቨርስቲ ውስጥ አገልግሎት   እንዲሁም  በማህበረሰብ አቀፍና ሙያዊ አገልግሎት እና  ለዓለም የዕውቀት ስርጸት መዳበር ስኬታማ አበርክቶ ላደረጉ መምህራን እና ተመራማሪዎች  መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም የኒቨርስቲው በሚመለከታቸው የትምህርት ክፍሎች ተመርመሮ፣ በየኮሌጆች አካዳሚክ ጉባዔዎች ተፈትሾ፣ በዩኒቨርስቲው ሴኔት ታይቶ እና ይሁንታ አግኝቶ የቀረበለትን መረጃ የተመለከተው የዩኒቨርስቲው የሥራ አመራር ቦርድ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፅድቋል።

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው  ዶክተር ይልማ ስለሺ ፣  ዶክተር አለሙ መኮንን ፣  ዶክተር አለማየሁ ገዳ ፣ ዶክተር በርሲሳ ኩምሳ ፣ ዶክተር ገበየሁ ጎሹ ፣  ዶክተር ሙሉጌታ አጥናፉ ፣ ዶክተር ጌታቸው ተረፈ ፣  ዶክተር አሰፋ ፍስሃ ፣  ዶክተር  ንጋቱ ከበደ ፣  ዶክተር  ግርማ ዘርአዮሐንስ ፣  ዶክተር  ሽመልስ አድማሱ  እና  ዶክተር አታላይ አየለ  መሆናቸውን ከዩኒቨርስቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለተሰጣቸው ለአስራ ሁለቱ መምህራንና ተመራማሪዎች፣ የትምህርት ክፍሎቻቸው፣ የሥራ ባልደረቦቻቸውና ቤተሰቦቻቸው እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ደስታውን ገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.