Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በሁለቱ ክልሎች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ13 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በአፋርና በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ምግብ፣ አልባሳትና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረጉ።
 
ቢሮው ካደረገው የ13 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መካከል 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ደሴ ከተማ ላይ ርክክብ የተደረገ ሲሆን፥ቀሪው በተመሳሳይ ቀን ለአፋር ክልል እንደዲደርስ መደረጉ ተገልጿል።
 
ድጋፉን ያስረከቡት የገቢዎች ቢሮ የህግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር አህመድ መሀመድ እንደተናገሩት፥የቢሮው ሰራተኞችና አመራር ድጋፉን ያደረጉት በአፋርና በአማራ ክልል ከቤታቸውና አካባቢያቸው ለተፈናቀሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው።
በቀጣይም ቢሮው የተቻለውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ኃላፊው ጠቁመዋል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ውዴ ቴሶ በበኩላቸው፥ድጋፉ የተደረገው አሸባሪው የህወሓት ኃይል የጎዳቸውና ያፈናቀላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ወገን እንዳላቸው ለማሳየት ነው።
“ድጋፉ ኢትዮጵያዊ አንድነት የጠነከረና የተሳሰረ መሆኑን ያሳያል፤ ከመከላከያ ሠራዊት ጎን መሠለፋችንን ያመለክታል፤ውድቀትና ሞት ለአሸባሪው የሕወሓት ቡድን፤ ድልና ብልጽግና ለኢትዮጵያ ይሁን” ብለዋል።
 
የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል፥በወረራ ጊዜ ከፍተኛ ሰቆቃ የደረሰበት ማሕበረሰብ በጀግናው መከላከያ ሰራዊት ነጻ መውጣት ችሏል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከተሰጠው ተልዕኮ ባሻገር ጦርነቱ ያስከተለውን ዘርፈ ብዙ ችግር በመገንዘብ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።
በጦርነቱ በርካታ ማሕበረሰብ መገጎሳቆሉንና መጎዳቱን አስታውሰው፤ የተገኘውን ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍ ችግረኞችን በመመልመል በፍትሃዊነት ለመድረሥ እንደሚሰራ መጠቆማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታርያት ኢፕድን ጠቅሶ ዘግቧል።
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.