Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ 22 ቢሊየን 647 ሚሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ስድስት ወራት 22 ቢሊየን 647 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።

ቢሮው የስድስት ወራት አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት ነው የሰበሰበውን ገቢ ይፋ ያደረገው።

ባለፉት ስድስት 24 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 94 ነጥብ 3 በመቶው ማሳካት እንደቻለ ተጠቁሟል።

ቢሮው የለውጥ ስራ በመስራቱ እና ብቃት ያላቸው ሴቶች ፈፀሚዎችን  ወደ አመራርነት ማምጣቱ ለዚህ ስኬታ አስተዋፅኦ ማበርከቱ በመድረኩ ላይ ተነስቷል።

እንዲሁም የህግ ተገዥነትን ለማስፈን  ህግን ለማስከበር ጠንካራ እርምጃዎችን መወሰዱ እና ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ማሻሻያ ማድረጉ ሌላኛው የስኬቱ ምክንያት ነው።

ቢሮ እቅዱን መቶ በመቶ ማሳካት ያልቻለው በደረሰኝ አለመቆረጥ እና ሀሰተኛ ደረሰኝ በሚጠቀሙ አካላት መሆኑ ተጠቁሟል።

በቀጣይ ህግ የማስከበር እርምጃውን በማጠናከር ከተማዋ መሰብሰብ በሚገባት ልክ መስብሰብ  እንድትችል እንደሚሰራ ተነግሯል።

በሲሳይ ወርቁ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.