Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፖሊሳዊ የደንብ ልብስና ዓርማ መቀየሩን ምክንያት በማድረግ የማብሰሪያ መርሀ-ግብር አዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ፖሊሳዊ የደንብ ልብስና ዓርማ መቀየሩን ምክንያት በማድረግ የማብሰሪያ መርሀ-ግብር ሊያካሂድ መሆኑን ገለፀ፡፡
ይህን ተከትሎ በዕለቱ ልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች የሚከናወኑ በመሆኑ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ድረስ የተወሰኑ መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ ነው የተባለው፡፡
በዚህም መሰረት ከኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ፣ከ4ኛ ክፍለ ጦር/ጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ፣ከሀራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ፣ከለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ፣ከብሄራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱና በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ መጋቢ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
አሽከርካሪዎችም አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.