Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ነዋሪዎች ለተፈናቃዮች 15 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የአይነትድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በአሸባሪው ህወሓት ተፈናቅለው ሰሜን ወሎ ዞን በመጠለያ ካፕ ለሚገኙ ወገኖች ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በክፍለ ከተማው የቴክኒክ ሙያ ስልጠና ቴክኖሎጅ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጀማል መሀመድ÷ የሽብር ቡድኑ ህወሓት በዜጎች ላይ የፈጸመው ዘገናኝ ድርግት እና እኩይ ሴራ የሚያሳዝን መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ክፍለ ከተማው ከባለሃብቶችና ከሌሎች አካላት ያሰባሰበውን ከ15 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጪ የምግብ እህልና ቁሳቁስ ለተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

የተፈናቃዮቹ ሁኔታ እንቅልፍ የሚነሳ በመሆኑ ከዚህ በፊትም በዞኑ መቄት ወረዳ ተገኝተው ድጋፍ እንዳደረጉና በቀጣይም ችግሩ እስኪፈታ ተጨማሪ ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉ አቶ ጀማል ተናግረዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር በበኩላቸው ÷የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በዞኑ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ሁሉም ዜጋ የሚችለውን በመደገፍ ከወገኖቹ ጎን መቆም እንደሚገባም ማሳሰባቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተለይም በዞኑ ሀብሩ ወረዳ ድሬ ሮቃ ጃራ መጠላያ የሚገኙ ወገኖቻችን የከፋ ችግር ላይ በመሆናቸው ሁሉም ሰው ርብርብ እንዲያደርግና የምግብ ድጋፍ እንዲድረግላቸው ሃላፊው ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.