Fana: At a Speed of Life!

የአዳዲስ ክልሎች መዋቀር መንግሥት ፀረ ፌደራሊዝም አለመሆኑን ያሳያል – ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ መንግሥት ፀረ ፌደራሊዝም አለመሆኑን በተግባር እያሳየ ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ÷ 11ኛ ክልል ሆኖ ዛሬ የተደራጀውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምስረታ በማስመልከት በማህበራዊ ገጻቸው የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም÷ ለውጡ ከመጣ መጋቢት 2010 ወዲህ ይህ ሁለተኛው አዲስ ክልል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ሲዳማ 10ኛ ክልል ሆኖ መደራጀቱን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ይህም የፌደራሉ መንግሥት ፀረ ፌደራሊዝም ነው በሚል የሚሰነዘርበትን ወቀሳና የሐሰት ትርክት ውድቅ የሚደርግ ነው ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.