Fana: At a Speed of Life!

የአገራችንን ህልውና ለማስቀጠል ሁሉም የድርሻውን ይወጣ -የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ ከስሩ ለመንቀል ሁሉም በየመክሊቱ የድርሻውን አስተዋጽኦ ሊያደርግ እንደሚገባ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ ገለጹ፡፡

ሚኒስትር ዲኤታዋ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት ÷ወቅቱ የህልውና ጦርነት እየተካሄደ ያለበት ጊዜ በመሆኑ ስለ ኢትዮጵያ ያገባኛል የሚል ሁሉ ባለበት ቦታ እና በየፊናው ለኢትዮጵያ ህልውና አሻራውን ማስቀመጥ አለበት፡፡

በሌሎች የዓለም ክፍሎች ኑሯቸውን ያደረጉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለህልውና ዘመቻው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነ እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ስኬታማ የ”በቃ” (No more) እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

ይህም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ንቅናቄ መፍጠሩን ለማየት ማስቻሉን በመጥቀስ፥ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚሰሩ እና ትላልቅ ተጽእኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን ባሉበት እና ተጽዕኖ መፍጠር በሚችሉበት መንገድ ሁሉ የኢትዮጵያን እውነት ለመላው ዓለም በማሳወቅ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የመገናኛ ብዙሃንም ተደራሽነታቸውን ለማስፋት እንዲያስችል በተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ቋንቋዎች ከመጠቀም በተጨማሪ እውነተኛና የተረጋገጠ ፈጣን መረጃ ለአድማጭ ተመልካች በማድረስ ህብረተሰቡን በሃሰተኛ መረጃ እንዳይወናበድ የማድረግ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ህብረተሰቡም በየዩቲዩብ የሚለቀቁ መረጃዎችን ማመን የለበትም ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የጦርነት ወቅት ተግባቦት በጣም ጥንቃቄ የሚፈልግ መሆኑን በመገንዘብ የአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች የተመለከቱ ፈጣን እና የተረጋገጡ መረጃዎች በየሳምንቱ ለህብረተሰቡ እያደረሰ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

በአመለወርቅ ደምሰው

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.