Fana: At a Speed of Life!

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ካቢኔ አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገራዊ  ምክክር ኮሚሽነሮች ከሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የካቢኔ አባላት ጋር ተወያዩ፡፡

በምክክር መድረኩ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያን ጨምሮ ሌሎች የኮሚሽኑ አባላት፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የካቢኔ አባላት ተሳትፈዋል፡፡

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ÷ኮሚሽኑ ከተቋቋመ በኋላ ባለፉት ሶስት ወራት የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ገለጻ አድርገዋል።

መድረኩ በቀጣይ ለሚከናወነው የኮሚሽኑ ስራ ክልሎች የሚኖራቸው ድርሻ ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

በቀጣይም ከወጣቶች እንዲሁም ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እንደሚወያዩ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.