Fana: At a Speed of Life!

የአፈፃፀም ውስንነት ባለባቸው አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል-አቶ ሱልጣን አብዱሰላም

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፈፃፀም ውስንነት ባለባቸው አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም ገለጹ።
 
የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም የምክር ቤቱን የቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን በተመለከተ መግለጫ ሰተዋል፡፡
 
በመግለጫቸውም ምክር ቤቱ ከሚያከናውናውቸው ስራዎች መካከል ለህዝብ ጥቅም እንዲውል የተመደበ በጀት በትክክል ስራ ላይ ስለመዋሉ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በመሆኑም በተለይ በዘንድሮው የበጀት አመት ከሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር የልማት ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ ማከናወን ይገባል ብለዋል፡፡
 
ከዚህ አንፃርም የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ከታህሳስ 19 ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 19 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የመስክ ምልከታ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
ስለሆነም ተቋማት በመጀመሪያ ሩብ አመት የተከናወኑ ተግባራት በሚመለከት የመስክ ምልከታ እንደሚያደርግ ተገንዝበው ያከናወኗቸውን ተግባራት ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ማስቃኘት ይገባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።
 
ከመስክ ምልከታው በኋላም መልካም ተግባራትን በማበረታታት እና ክፍተት ባሉባቸው ተቋማት ላይ ተገምግሞ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰወድ መግለጻቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.